Page 167 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 167
አብን
ይሰራበታል፡፡ የጤና አሰጣጥና አተገባብር ሂደቶች ክትትልና
መረጃ ለውሳኔ ትኩረት ይደረግባታል፡፡
አመራርና አስተዳደር
የጤናው ዘርፍ አመራርና አስተዳድር የዘመነ እንዲሆን
ይደረጋል፡፡ በሚኒሰቴር ደረጃ የሚመራ ቢሆንም የጤናው
ዘርፍ ብቁና የተነቃቃ አመራር እንዲኖረው የጤናው
ቴክኖክራት በውድድር የሚቀጠር ሆኖ በሚኒሰቴር ዴኤታ
ደረጃ አስተዳድራዊ መዋቅሩ እንዲመራ ይደረጋል፡፡ የሚኒሰቴሩ
የበላይ ፖለቲካዊ ኃላፊነት ሲኖረው የዕለት ከዕለት አገልግሎቱ
ግን በውድድር በሚቀጠር ባለሙያ እንዲመራ ይሆናል፡፡
በየደረጃውም ተጠያቂነትን ያማከለ ጠንካራ አመራር እንዲኖር
ይደረጋል፡፡
የዘርፈ ብዙ ምላሽ እና የተጓዳኝ ሁነቶች
በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ የዴሞግራፊያዊና የጤና
ሁነት ለውጥ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን ላይ
የሰው ልጅ ዕድሜ በአማካኝ ከ70 ዓመት በላይ እንደሆነ
ይገመታል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለሰው ልጅ የጤና
ተግዳሮት የነበሩት ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች፣ የምግብ እጥረት
እና የእናቶችና ሕፃናት ሞት አመርቂ በሚባል ደረጃ የተቀረፉ
ቢሆንም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የእነርሱ አጋላጭ
መንስዔዎች ደግሞ በአንፃሩ ሥር የሰደዱ የጤና ተግዳሮቶች
በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ 71 በመቶ የሚሆነው የዓለም
165 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !