Page 199 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 199
አብን
ያላቸው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በእርስ በእርስ ጥርጣሬ፣ ጥላቻና
በቀል ስሜት ተፋጥጠዋል፡፡ በአገሪቱ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ
በማይታወቅ ሁኔታ ዜጎች የመኖር ዋስትናቸው የተገፈፈበት፤
ግድያ፣ስደትና የኃብት ውድመት የተፈፀመበት በመሆን አስከፊ
ታሪካዊ ጠባሳን እንዳኖረብን መካድ አይቻልም፡፡
አብን የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ በሐሠተኛና በተንሻፈፈ
የጥላቻ ትርክት ላይ የተነደፈው ሕገ-መንግሥት፣ በዚህ ላይ
የተገነባው የፌደራል ሥርዓት አወቃቀርና በአጠቃላይ አገራዊ
አንድነትን አደጋ ላይ የጣለው የሕወኃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ
መሆኑን አበክሮ ይገነዘባል፡፡ ይህ ሥርዓት በጥልቅ/በስር
ነቀልነት የሚሻሻልበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር አገዛዙ
ለይስሙላ እራሱን ቢያድስና የአስተሳሰብ ለውጥ አመጣ ቢባል
እንኳ የአገሪቱንና የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ
ከቶውንም እንደማይቻለው ያምናል፡፡
4.1.2. አብን አገራዊ ሠላም፣ ደኅንነትና መረጋጋትን
ለማምጣት የሚከተላቸው ዋና ዋና ተግባራት
አብን ከሁሉም በፊት ሥርዓት ሰራሹን አገራዊ ቀውስና ይህም
ላለፉት አስርት ዓመታት በሕዝባችን መካከል የፈጠረውን
ቁስል ማዳንና ጠባሳውንም ማጥፋት ተቀዳሚ ተግባር መሆን
እንዳለበት ያምናል፡፡ በመሆኑም አስተማማኝ ሕዝባዊ ሰላምንና
ውስጣዊ መረጋጋትን ለመፍጠር እንዲሁም ሕዝባዊ አንድነትን
ለማጠንከር ‹‹ብሔራዊ እርቀ-ሰላምና መግባባት›› አስፈላጊ
መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ስለዚህም ንቅናቄአችን የአገር ሰላምና
197 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !