Page 75 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 75
ከእንሰሳት ዓለም
ጥንቸል
ጥንቸል የአጥቢ እንስሳ አይነት ነው።
በኢትዮጵያ መንትሌ የሚባል ጥንቸል የሚመስል ፍጡር አለ። ጥንቸልና
መንትሌ በጣም ስለሚመሳሰሉ በኢትዮጵያም ውስጥ መንትሌ የምትባል
አይነት ብቻም ስለሚገኝ በተራ አነጋገር እነዚህ ስሞች ተለዋውጡ
እንጂ ሁላቸው አንድ ናቸው። «መንትሌ» ወይንም «ጥንቸል» ሊባሉ
ይችላሉ።
በሥነ ሕይወት ረገድ ግን በጥንቸልና መንትሌ መሃል ልዩነት አለ። ይህም
ልዩነት በደንብ «ጥንቸሎች» የሚባሉት በምድር ውስጥ ሲኖሩ ያለ
ጽጉርና ዕውር ሆነው ይወለዳሉ። «መንትሌዎች» ግን ከምድር በላይ
ሲኖሩ ባለ ጽጉርና በጥራት አይተው ይወለዳሉ። በዚህ አከፋፈል ዕውነተኛ
«ጥንቸል» የምትባል በኢትዮጵያ ውስጥ አትገኝም። አንዳንድ ዕውነተኛ የጥንቸል
ዝርያ ግን በደቡባዊ አፍሪካ አለ።
አንዱ የጥንቸል ዝርያ እሱም የአውሮፓ ጥንቸል በሰው ልጆች ለማዳ ጥንቸል ተደርጓል።
DINQ magazine June 2020 #209 PLEASE BE SAFE and Happy Father's Day Page 75