Page 61 - Descipleship 101
P. 61
ጸሎትና ክርስቲያን
ብዙ ሰዎች እንዴትና ለምን እንደሚጸልዩ ባያውቁም መጸለያቸውን አይተውም፤ በዚህም ምናልባት ሰው መንፈስ እንዳለውና ከእንስሳት የተለየ መሆኑን እንረዳለን። ሰው በተጨነቀ ጊዜ ወደ እግዚአብሄር ሲጮህ እንስሳት ግን ይህ ባህርይ እንዳላቸው የምናውቅበት መንገድ የለም። የማያምኑ ሰዎችም እንኳን በችግራቸው ጊዜ ይረዳናል ብለው ወደሚያስቡት አምላክ ይጸልያሉ። ዮናስን እንኳን ወደ ባህር የጣሉትን መርከበኞች ዮናስን ከመጣላቸው በፊት ጸልየው ወደየራሳቸው አማልክት ጸልየው ነበር (ዮናስ. 1፡14-16)። እግዚአብሄር ወደ እርሱ የሚጮሁትን ስለ ኃጢአታቸውም ንስኀ የሚገቡትን ይሰማቸዋል። እውነተኛና ትክክለኛ ጸሎትን የሚጸልዩ ግን ዳግም የተወለዱ አማኞች ብቻ ናቸው።
የጸሎት ምሳሌዎች
በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ብዙ የጸሎት ምሳሌዎች አሉን። ሰዎች ወደ እግዚአብሄር መጸለይ የጀመሩት በሴት ዘመን ነው (ዘፍ፡26)። በራእይ መጽሀፍም ላይ መንፈሱና ሙሽራይቱ (ቤ/ክ) ና እያሉ ወደ ክርስቶስ እንደሚጸልዩ እንመለከታለን (ራዕ.22፡17- 20)። በብሉይ ኪዳን ነቢያት ካህናትና ነገስታት ጸልየዋል።
የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብና ማን ይጸልይ እንደነበር ጻፍ።
60