Page 62 - Descipleship 101
P. 62

1. 1ሳሙ.12፡23--------------------------------------------------
2. ዘኁ. 6፡24----------------------------------------------------
3. 1ዜና. 17፡25--------------------------------------------------
አብርሃም ሆነ ሌሎች የእስራኤል መሪዎች ሙሴ፣ ኢየሱ፣ሰለሞን፣ኤልያስ፣ ዳንአልና ነህምያ በዘመናቸው ይጸልዩ ነበር። በአዲስ ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ በጸሎት ከአባቱ ጋር ይነጋገር ነበር። ጌታን የሰው ልጅ መሆን በሚገልጸው በሉቃስ ወንጌል ላይ ጌታችን ሰባት ጊዜ ሲጸልይ እንደነበር ተጽፎአል። በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ መድኃኒታችን ወደ አብ ይጸልይ ነበር። በሉቃስ ወንጌል እንደተጠቀሰው ጌታችን ሲጠመቅና (ሉቃ. 23፡2) ነፍሱን በመስቀል ላይ እያለ ለአባቱ ሲሰጥ (ሉቃ.23፡46) የጸለየውን ጸሎት እንመለከታለን።
የጸሎትን ንድፍ (pattern)
ጌታችን ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ትክክለኛ ንድፍ ሰጥቶናል (ማቴ.6፡9-13)። ይህን ጸሎት ዝም ብለን እንድናነበው ወይንም እንድናነበንበው የተሰጠን አይደለም። በመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን እንደዚህ አላደረጉም። ጌታ ይህንን ጸሎት ያስተማረው ብዙ ዋና ዋና ነገሮችን እንድናስተውል ነው።
1. ጸሎታችንን በአምልኮ መጀመር አለብን (ቁ.9)።
2. በመጀመሪያ ስለ እግዚአብሄር ስራ እና ክብር
61


























































































   60   61   62   63   64