Page 64 - Descipleship 101
P. 64
የት እንጸልይ?
በማንኛውም ስፍራና ቦታ መጸለይ ይቻላል። በአዲስ ኪዳን ጸሎት የተለየ ስፍራ የለንም። አምላካች በስፍራ ሁሉ የሚጸለይን ጸሎት ይሰማል። ነገር ግን ሃሳባችን እንዳይበታተን ጸጥታ ያለበት ስውር ስፍራ ይመረጣል (1ጤሞ. 2፡8)።
እንዴት እንጸልይ?
ክርስቶስ መስቀል ላይ ከመሞቱ በፊት የቤተመቅደስ መጋረጃ ሰውን ከቅዱስ እግዚአብሄር ለይቶት ነበር (ሉቃ.1፡10)። ሙሴ እግዚአብሄርን ሊያነጋግር ወደ ጨለማው በቀረበ ጊዜ እስራኤል ግን ርቀው ቆመው ነበር (ዘጸ. 20፡21)። ነገር ግን ጌታችን በመስቀል ላይ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ የቤተመቅደስ መጋረጃ ስለተተረተረ ከእንግዲህ የአዲስ ኪዳን አማኞች በርቀት መቆም አይገባቸውም። እግዚአብሄርም ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይጋብዘናል (ዕብ. 10፡19- 22)። እያንዳንዱ አማኝ በቀጥታ በጌታ በኢየሱስ በኩል በመንፈስ ቅዱስ ወደ አብ የመቅረብ መብት አለው።
“ በእርሱ ስራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለና። ” ኤፌ. 2፡18
እግዚአብሄር አብ ልጁ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን በከፈለው ዋጋ ስለረካ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋን ለመቀበል ወደ ዙፋኑ ልንቀርብ እንችላለን (ዕብ. 4፡16)። ያለ ፍርሃት ወደ ዙፋኑ መቅረብ እንደምንችልና በትህትና መቅረብ እንደሚገባን መዘንጋት የለብንም። የሰማዩ አባታችን የዘላለም አባት ስለሆነ በአክብሮትና 63