Page 66 - Descipleship 101
P. 66

በምንጸልይበት ጊዜ በአጠቃላይ ሳይሆን በተብራራ መንገድ የምንፈልገውን ለእግዚአብሄር መንገር ይገባናል። ለምሳሌ ጴጥሮስ በታሰረ ጊዜ በቤተክርስቲያን ስለ ጴጥሮስ አጥብቆ ይጸለይ ነበር (ሐዋ.12፡5)። እግዚአብሄር ወዲያውኑ ጸሎታችንን ባይመልስልን እንኳን እስኪመልስልን ድረስ በትእግስት ልንጸልይ ይገባናል (ሉቃ.11፡5፣ ሉቃ.18፡1-8)።
የማይመለስ ጸሎት
እግዚአብሄር የምንጸልየውን ጸሎት ሁሉ አይመልስም። የሚመልሰውም ደግሞ ሁልጊዜ እኛ በምንፈልገው መንገድ ላይመጣ ይችላል፤ መርሳት የሌለብን እግዚአብሄር አሁኑኑ ባይመልስ እንኳን በጊዜውና በሰዓቱ እንደሚመልስ ነው። እግዚአብሄር ስለሚወደን ለኛ የሚጠቅመንን አስቦ ይሰጠናል።
“የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለች። ”ያዕ.5፡6 የአማኝ ጸሎት የማይመለስበት ምክንያቶች
• ያልተናዘዘው ኃጢአት በሕይወቱ ውስጥ ካለ - ኢሳ. 59፡1- 2፤ መዝ (66፡18)፤ ዮሐ. 3፡20-22
• ሌሎችን ይቅር አለማለት - ማር. 11፡25-26
• ለራሱ የሚመቸውን ብቻ ከጸለየ-ያዕ. 4፡3
• በትዳር ውስጥ ያልተፈታ ነገር ካለ - 1ጴ.3፡7
• ያለ እምነት የሆነ ጸሎት ከጸለየ- ያዕ. 1፡6
• ጌታ እንጂ እኛ በማናውቀው ምክንያት 65
 
























































































   64   65   66   67   68