Page 68 - Descipleship 101
P. 68
ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና። እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፤ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ስራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በስጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ። ይህም ተመስርታችሁ ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፤ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ። አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተክርስቲያን በስጋዬ በክርስቶስ መከራ የጎደለውን እፈጽማለሁ። ”
2. በአንድ ቦታ የሚገኙ አማኞች ሁሉ ይህች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ናት።
ምሳሌ፤ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን፣ የሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን፣ ቀራንዮ ቤተ ክርስቲያን፣ የጽዮን ክብር ቤተ ክርስቲያን በቫንኩቨር ወዘተ።
የቤተ ክርስቲያን አጀማመር
ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ በብሉይ ኪዳን ጊዜ ግን በምድር ላይ አልነበረችም። በበዓለ ኀምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ በወረደ ጊዜ ቤተክርስቲያን ወደ መገኘት መጣች ወይንም ተመሰረተች። እግዚአብሄር ቤተ ክርሰትያንን ለመመስረት ዕቅድ ነበረው ነገር ግን ይህ መለኮታዊ ዕቅድ ባለፉት ዘመናት ሁሉ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነበር (ቆላ.1፡24-26)።
“ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፤ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሄር ከዘላለም የተሰወረው የሚስጥር
67