Page 67 - Descipleship 101
P. 67
ቤተክርስቲያን
ብዙ ሰዎች ስለ ቤተክርስቲያን ምንነት የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፤ ቤተ ክርስቲያን ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ ሜቶዲስት፣ ባፕቲስት ወይንም ኦርቶዶክስ የሚለው የቤተ እምነት መለያ ወይም የመሰብሰቢያ ቦታ (ቤት) ይመስላቸዋል። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ አመለካከት አይደለም። በግሪክ ቋንቋ ቤተክርስቲያን (Ecclesia) ማለት ከብዙዎች መካከል ተጠርተው የወጡ ሰዎች ሰብሰብ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስም ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው ከአለም ተጠርተው ጌታችንና መድኃኒታችንን በሚከተሉ ሰዎች ነው።
ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ምስክር ስለሆነች አለም ቤተ ክርስቲያንን አትቀበልም። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ላልዳኑ ሰዎች ክምችት ወይንም ለድርጅት መጠሪያ ልትሆን አይገባም። አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ቃል በሁለት መንገድ ይጠቀምበታል።
1. በምድር ላይ ላሉ አማኞች ሁሉ-ይህች የክርስቶስ አካል ተብላ የምትጠራው አለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን ናት። ቆላ.1፡18-24
“እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፤ መጀመሪያ ከሙታንም በኩር ነው።
እግዚአብሄር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፤ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን 66