Page 65 - Descipleship 101
P. 65

በመንቀጥቀጥ (መዝ.89፡6-7) በንጹህ እጅና በንጹህ ልብ ልንቀርበው ያስፈልጋል።
“ወደ እግዚአብሄር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ ልቡም ንፁህ የሆነ፤ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሳ.......” መዝ. 24፡3-4
መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ልብ ስላለው ሸክም በማይነገር መቃተት እንደሚማልድ መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል (ሮሜ.8፡23፣26-27)። ስለዚህ ምንግዜም ጸሎታችንን በመንፈስ ቅዱስ መመራትና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል መጸለይ ይገባል (ኤፌ.6፡18)። ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የምንጸልየው ነው እንጂ ሰው የጻፈውን የጸሎት መጽሀፍ ማንበብ ወይንም ማነብነብ አይደለም። ስንጸልይ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም መጸለይ አለብን (ዮሐ.14፡13- 14)።
ይህም ማለት ለጸሎት መዝጊያ ያህል እንዲሁ “በኢየሱስ ስም አሜን” ማለት ብቻ ሳይሆን በስሙ መጸለይ ማለት በኢየሱስ ስልጣንና ፈቃድ መጸለይ ማለት ነው። ይህ የሚሆነው ደግሞ የምንጸልየው ጸሎት ከተጻፈው ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ሲስማማ ነው (1ዮሐ.5፡14-15)። ሌላ ማስታወስ ያለብን ነገር እግዚአብሄርን በየዕለቱ ኑሮአችን ስንታዘዝ እርሱ ደግሞ ጸሎታችንን እንደሚመልስ ነው።
“በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ለምኑ ይሆንላችኋል።” ዮሐ.15፡7
64





























































































   63   64   65   66   67