Page 69 - Descipleship 101
P. 69
ስርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፤ ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሄር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ስልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘላለም ሃሳብ ነበረ። ” ኤፌ.3፡9-11
መጀመሪያ ስለ ቤተክርስቲያን የተናገረው ጌታ ኢየሱስ ነበር።
“እኔም እልሃለሁ፡ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህች አለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፤ የገሀነብ ደጆችም አይችሉአትም። ” ማቴ. 16፡18
“ጌታ ኢየሱስ ቤተክርስቲያኔን እመሰርታለሁ” ማለቱ በዚያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ገና እንዳልተመሰረተች ያሳየናል ይህ ጥቅስና ማቴ. 18፡17 ብቻ ከወንጌላት ውስጥ ስለቤተክርስቲያን ይናገራሉ። በሐዋ.2፡23 እግዚአብሄር አብ ኢየሱስን ካከበረው በኋላ ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ እናነባለን። በሰማይ ራስ ከሌለ በምድር የክርስቶስ አካል ሊኖር አይችልም። ክርስቶስ በሰማያት በራስነት በተቀመጠ ጊዜ በምድር ላይ የአካሉ (የቤ/ክ) ልደት ሆነ። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ልደት በዓለ ኅምሳ ነበር ብንል አንሳሳትም (ኤፌ.1፡20-23)።
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት
ቤተክርስቲያን እንደ መንግስት ወይንም እንደ ፋብሪካ ድርጅት ወይንም ህንጻ አይደለችም። ቤተክርስቲያን ህያው አካልና በውስ ጧም እውነተኛ አማኞችን አቅፋ የያዘች ናት። ይህ እውነት የቤተክርስቲያንን ምንነት ይገልጣል።
68