Page 71 - Descipleship 101
P. 71

“ሃሌሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሶአልና። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድር
ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ። ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጎናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን የጽድቅ ስራ ነውና” ራዕ. 19፡7-9
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል በሌላም ስፍራ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል። ይህም በአንድ አካባቢ የሚኖሩትን አማኞች ለማሳየት ነው። ለምሳሌ “የገላትያ ቤተ ክርስቲያን” (ገላ.1፡2)፤ በይሁዳ ለምትገኝ የእግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያን (1ተሰ.2፡14፤ 1ቆሮ.11፡16፤ ሮሜ. 16፡4፣16። )።
አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድርጅት ቅርጽ ቢኖራቸውም ድርጅቶች አይደሉም፤ የጋራ ራስ ያላቸው ናቸው። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የሚመሩትም በመንፈስ ቅዱስ ነው። አላማቸውም አንድ ነው ያም እንደ ብርሃን እየተመላለሱ ክርስቶስን መመስከርና ለሌሎች እውነቱን መናገር ነው (ፊል.2፡15-16)።
በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እነማን አሉ?
በፊልጵስዮስ በነበረችው ቤተክርስቲያን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ምዕመናን፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና ረዳቶች ነበሩ (ፊል.1፡1)። በመጀመሪያ ሁሉም አማኞች በአንድ ስፍራ ኅብረት ነበራቸው፤ ነገር ግን በዚህ ዘመን ሁሉም እውነተኛ አማኞች በዚህ ዘመን ሁሉም እውነተኛ አማኞች በዚህ ዘመን በተለያዩ አብያተ
 70



























































































   69   70   71   72   73