Page 70 - Descipleship 101
P. 70
• በኤፌ.1፡23 ላይ እንደ አካል (body) - ህያውነቷን
• በኤፌ 5፡25 ላይ እንደ ሙሽራ - ለኢየሱስ ያላትን ፍቅር
• በኤፌ. 2፡20 ላይ እንደ ህንጻ - የመኖርያ ቤትነቷን
መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ስለመሰረተ (1ቆሮ.12፡13) አንድነትንም ደግሞ እርሱ ይሰጣታል (ኤፌ.4፡3)፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራሷ (መሪዋ) ነው።
“እርሱ የአካሉ ማለት የቤተክርስቲያን ራስ ነው። ” ቆላ. 1፡18 ወደፊት ቤተክርስቲያን ምን ትሆናለች?
“እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ”
እግዚአብሄር አምላካችን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ክብር ለዘላለም እንድትካፈል አቅዷል። ኢየሱስ ክርስቶስም ቤተ ክርስቲያንን ያለምንም ነውርና ነቀፋ ሆና እንድትቀርብ ወደ እርሱም ሊወስዳት ይመጣል (ኤፌ.5፡27)። በዚያ ጊዜ ታላቅ ደስታ በሰማያት በበጉ ሰርግ ጊዜ ይሆናል።
69