Page 72 - Descipleship 101
P. 72
ክርስቲያናት ውስጥ ቢሆኑም አንድ አይነት አስተሳሰብና አምልኮ አላቸው። ማንኛውም እውነተኛ ክርስቲያን በአለበት ስፍራ የክርስቶስ አካል አባል ነው።
በቤት ውስጥ የሚሰበሰቡ ጥቂት አማኞች ቤተ ክርስቲያን ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ (1ቆሮ.16፡19፤ ቆላ.4፡15)። በየትም ስፍራ ያለች ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ዙፋን ስር ትሰበሰባለች። ክርስቶስም ሁለትም ሆነ ሶስት በስሙ በተሰበሰቡት ስፍራ ይገኛልና (ማቴ. 18፡2)።
የክርስቶስ አካል የብዙ እውነተኛ አማኞች ስብስብ ነው። እኛ የእርሱ አካል /body/ አባላት ነን፤ በህይወት መጽሐፍ የተጻፉ እነዚህ ብቻ ናቸው። የጌታ ራት የዚህ አንድነት ምሳሌ ነው (1ቆሮ.10፡16-17)። መንፈስ ቅዱስ የአንዲት አጥቢያ ቤተክርስተያን አባላት በአምልኮና በቃሉ ትምህርት ይመራል። የቤተ ክርስቲያን መጋቢ ሽማግሌዎችና ይህንን ስብሰባ ስርዓት የማስያዝና በኃጢያት የወደቀውን ሰው የማረም ኃላፊነት ያለባቸው አገልጋዮች ናቸው።
የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ዓላማ (purpose)
ራእይ 1፡20 ላይ የምንመለከተው የወርቅ መቅረዝ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው። ወርቅ መለኮታዊ ቅድስናን ሲያሳይ መቅረዝ ደግሞ ቤተክርስቲያንን ለዚህ አለም ብርሃን መሆንና ስለክርስቶስ መመስከሯን ያሳያል። የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ዓላማ ይህችን አለም የተሻለ የመኖሪያ ቦታ ለማድረግ ሳይሆን የዚህን አለም ሰዎች ክርስቶስን ለማስተዋወቅና ሰዎች ሁሉ አምነው እንዲድኑ
71