Page 149 - አብን
P. 149
አብን
የኢትዮጵያ የውኃ ኃብት ልማት ፓሊሲ መሰረታዊ
ችግሩ የቆየውን ነባራዊ ሁኔታ የማስጠበቅ አዝማሚያ
ያለው መሆኑ ነው፡፡ ይህም በውኃ ኃብት ልማት ዘርፉ
መንግስት ዋነኛ ኢንቬስተር፣የውኃ ፕሮጀክቶች
ተግባሪና አስተዳዳሪ ሆኖ መቀጠሉ ነው፡፡ የመንግስት
ድርሻ በዚህ ደረጃ ከፍተኛ በሆነበት ሁኔታ የውኃ
አቅርቦት ችግሩን መቅረፍ አይችልም፡፡ ስለዚህ የአማራ
ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የውኃ ኃብት ልማት ፓሊሲ
መንግስት በውኃ ልማት ዘርፉ ያለውን የገዘፈ ሚና
እንዲቀንስ በማድረግ የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍበት
ያደርጋል፡፡ መንግስት ሁሉንም የውኃ አገልግሎት
ከመስጠት ወጥቶ ወደ ማስተባበር፣ አቅጣጫ
ማስያዣና የሕግና ቁጥጥር ሥርዓት ወደ መምራት
እንዲያተኩር ይደረጋል፡፡
የውኃ ኃብት እንክብካቤያችንና የልማት አቀራረባችን
ከፍተኛ የሆነ የቅንጅት ችግር አለባቸው፡፡ስለዚህ
የሚተገበሩ የውኃ ልማት ፕሮጅክቶች በተቀናጀ
መንገድ እንዲተገበሩ ያደርጋል፡፡የመጠጥ ውኃ፣ የፍሳሽ
ማስወገድ፣ ጤናና ንጽህና ሥራዎች በተቀናጀ መሰረት
የሚተገበር መሆን አለበት፡፡
የውኃ ኃብት ልማት ሥራዎች የተለያዩ ዘርፎችን
ፍላጎት (sectoral demand) መሰረት ያደረገ
(የመኖሪያ ቤቶች፣ የኢንዱስትሪ፣ የእርሻው ዘርፍና
የተፈጥሮ ፍሰት ፍላጎቱን (environmental flow
147 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !