Page 154 - አብን
P. 154
አብን
agriculture) መጠቀም መጀመር ያስፈልጋል፡፡
እንደእስራኤል ያሉ አገሮች በትንሽ ውኃ ብዙ ምርት
ማምረት የሚችሉበትን እንደ የጠብታ መስኖ አይነት
ውኃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂ ሊያግዙ የሚችሉ
እንደፒቪሲፓይፓችንና ታንከሮችን የሚያመርቱ
አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችን በየአካባቢው እንዲገነቡ
ያደርጋል፡፡
2.6.2 የኃይል ዘርፍ
የኃይል ልማት ጥቅል ዓላማ
የአብን የኃይል ልማት እቅድ አቅጣጫዎች የኢትዮጵያን ሙሉ
ፍላጎት ከማሳካት ባለፈ የቀጠናው አገራትን የኃይል ምንጮች
እና ትስስር ታሳቢ ያደረገ ይሆናል። በዚህም ለአየር ንብረት
ሁኔታ ተስማሚ የሆኑትን አማራጮች በመጠቀም የአገሪቱን
የታዳሽ ኃይል አቅም ታሳቢ በማድረግ ስብጥሩን በማሳደግ
አስተማማኝ የሆነ ኃይል ማቅረብ ዓላማው ያደረገ ነው።
የኃይል ልማት በራሱ ብቻውን የሚቆም ሳይሆን ለልዩ ልዩ
አገልግሎቶች ግብዓት የሚውል ነው። ስለዚህም ተጠቃሚዎች
ያላቸውን እድገትና ተለዋዋጭነት ታሳቢ ያደረገ የኃይል
ልማት እና አብሮ የሚለዋወጥ ተቋማዊ መዋቅሮችን
ማደራጀት ያስፈልጋል። ይህ የኃይል ልማት ተቋም ተጠሪነቱ
ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል።
አብን የሚመረተው ኃይል የተጠቃሚዎችን ፍላጎት በሚያረካ
እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የማምረቻ ዋጋውን ለመቀነስ
152 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !