Page 159 - አብን
P. 159
አብን
ሠ. ተጨማሪ አስፈላጊ ተቋማት
እነዚህ ተቋማት ከዋናው የኃይል ማመንጨት እስከ
ተገልጋዮች ማድረስን ከሚከውነው እና በየጊዜው እንደዘመኑ
ይሻሻላል ካልነው የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ውጭ
ያሉትን ይመለከታል።
የኃይል ጥናት ምርምር ተቋም
ይህ ምርምር ተቋም አገሪቱ ያላትን የኃይል የማምረት አቅም፤
የአካባቢውን እና ዓለምአቀፋዊውን የኃይል አጠቃቀም ዘዴ
ግንኙነት፤ የአገሩቱን የኃይል ማመንጨት፤ ማሰራጨት እና
ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮችን ከኃሳባዊ የጥናት እቅድ አንስቶ
የተግባር አፈጻጸም ላይ በቀጥታ የሚሳተፍ ይሆናል። አሁን
በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተበታተነ መልኩ የተቋቋሙ የኃይል
ጥናት ማዕከላትን በማስተባበር ከንድፈ ኃሳብ እስከ ተግባር
የኃይል ግንባታዎችን መምራት እና መፈጸም የሚችል
ይሆናል።
የተጠቃሚዎች ቦርድ
ይህ ቦርድ በማዕከላዊነት የተደራጀ ሁኖ እስከወረዳ ድረስ
መዋቅሩን የዘረጋ የተጠቃሚዎችን መብት እና ፍላጎት
ማስጠበቅ ታሳቢ ያደረገ ተቋም ነው። ይህ ቦርድ ተጠሪነቱ
ከወረዳ ጀምሮ በሚወከሉ ተጠቃሚዎች በሚመሰረተ ጠቅላላ
ጉባዔ ይሆናል። ተግባሩም የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት
የሚወስዱትን የታሪፍ ማሻሻያ፤ በኃይል አቅርቦት የሚከሰቱ
አደጋዎች ካሳ ይገባኛል ውዝግቦች እና ሌሎች በተገልጋዮች
እና አገልግሎት ሰጭዎች ማዕከል የሚደረግን ግንኙነት
የተገልጋዮን መብት ለማስጠበቅ ይሰራል።
157 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !