Page 161 - አብን
P. 161
አብን
ምዕራፍ ሶስት
ማኅበራዊ ዘርፍ
3.1. ጤና
ሀ. የጤና ዘርፍ ፖሊሲ
መሰረታዊ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት ሰብዓዊ መብት
ተደርጎ ሁሉም ዜጎች በጥራትና ፍትኃዊነት ተደራሽ እንዲሆኑ
ይደረጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው ለጤናው ምቹ በሆነ
አካባቢ የመኖር መብት አለው፡፡ የጤና ፖሊሲው የመኖሪያ
አካባቢ የጤና ተስማሚነትን፣ የሥርዓተ-ምግብ መሻሻልንና
የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ማዕከል በማድረግ
ለበሽታ መከላከልና ጤናን ማበልፀግ ሥራዎች ቅድሚያ
ይሰጣል፡፡ የጤናው ዘርፍ መከላከልን ቅድሚያ ሰጥቶ
የሚዋቀር ይሁን እንጂ የፈውስ (Curative)፣ፓሌቲቭ
(palliative) እና የተሐድሶ (rehabilitative) የጤና
አገልገሎቶችም በየደረጃው ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲሰጡ
ይደረጋል፡፡ ዘርፉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ድንገተኛ
የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎችንና ወረርሽኞችን እንዲሁም
ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መመከት የሚያስችል
እና የአእምሮ ጤናን የሚያበለፅግ የጤና ሥርዓት ሆኖ
እንዲገነባ ይደረጋል፡፡
159 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !