Page 165 - አብን
P. 165
አብን
ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጥራትና ደረጃቸውን ጠብቀው
አገልግሎት እንዲሰጡ ድጋፍና ክትተትል ይደረግላቸዋል፡፡
የጤና ባለሙያ የሰው ኃይል
በችሎታቸው የዳበሩ፣ በስነ-ምግባር የታነፁና በሞራል የተነቃቁ
አገራዊ ኃላፊነት መሸክም የሚችሉ የጤና ባለሙያዎችን
በማፍራት የጤናው ዘርፍ በማኅብረሰቡና በተገልጋዮች
ታማኝና እርካታን የሚያጎናፅፍ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የጤና
ባለሙያዎች ደረጃቸውንና ወቅቱን የጠበቀ የሙያ ብቃት
እንዲኖራቸው ለማድረግ ወቅታዊ የሙያ ምዘናና ክትትል
እንዲኖር ይደረጋል፡፡ የጤና ባለሙያዎች በሙያቸው
የሚረኩ፣ ስነ-ምግባር የተላበሱ፤ ለሕዝባቸውና ለአገራቸው
ታማኝና የተነቃቁ ሰራተኞች እንዲሆኑ አገሪቱ የምትችለውንና
የሚገባቸውን ክፍያና ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
የመድኃኒቶች፣ ክትባት፣ የላቦራቶሪ ፍጆታዎች እና የሕክምና
ቴክኖሎጂ
የጤናው ዘርፍ ሙሉ መሆንና እና ለማኅብረሰብ እርካታን
ማጎናፀፍ ካለበት የመድኃኒት እና ግብዓት አቅርቦቱ ጥራቱን
የጠበቀ፣ ያልተቆራረጠ እና አስተማማኝ መሆን ይኖርበታል፡፡
የመድኃኒትና ግብዓት አቅርቦት በጤና አገልግሎቱ ላይ የዋጋ
ግሽበት እንዳያስከትል መንግሰት የመድኃኒት ግዥና
ሥርጭትን በበላይነት ይቆጣጠራል፤ ያስተባብራል፡፡
163 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !