Page 168 - አብን
P. 168
አብን
ሕዝብ ወይም 52 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ጊዜ
በዓመት ለሞት የሚጋለጡት ተላላፊ ባልሆኑ ኅመሞች፤
አደጋዎች (የመኪና አደጋ ጨምሮ) እና ለእነርሱ አጋላጭ
በሆኑ ለምሳሌ በሲጋራ ጪስ፣ አልኮል መጠጥ፣ የሰውነት
ውፍረት፣ የአካል እንቅስቃሴ ጉድለት፣ ወዘተ. ምክንያት ነው፡፡
እነዚህና መሰል የዘመናችን የጤና ተግዳሮቶች ደግሞ በአጭሩ
የጤና ችግር ብቻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ የአገር ዕድገትና
ኢኮኖሚ ችግሮች ናቸው፡፡
በመሆኑም እነዚህን የዘመናችን ተግዳሮቶች በአስተማማኝ
ሁኔታ ለመቅረፍ በጠቅላይ ሚኒሰትር ወይም በፕሬዝዳነት
ጽ/ቤት የሚመራ የዘርፍ መስሪያ ቤቶችን በዘርፈ ብዙ ትብብር
የሚመራ አደረጃጀት እንዲዋቀር ይደረጋል፡፡ የጤናማ መኖሪያ
አካባቢን ለመፍጠር፣ የሥርዓተ ምግብ ሁኔታን ለማሻሻልና
የሕክምና አገልግሎቶችን በጥራትና ፍትኃዊነት ለሁሉም ዜጎች
ለማዳረስ የሚያስችል የተቀናጀ የፖሊሲ ማእቀፍም ተግባራዊ
ይደረጋል፡፡
የማኅበረሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ፣ ቅስቀሳና ውትወታ
(Advocacy)
ማኅብረስብ የጤና አገልግሎትና ግብዓት ተጠቃሚ ብቻም
ሳይሆን የጤና አምራች እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ማኅበረሰቡ
የዕለት ከዕለት የጤና አግልግሎትና የጤና ፖሊሲዎች ውሳኔ
ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የቅስቀሳና የማንቃት ሥራ
ይሰራል፡፡
166 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !