Page 166 - አብን
P. 166

አብን


             መድኃኒትና  ግብዓቶች  በአገር  ውስጥ  የሚመረቱበትን  ሁኔታ

             ያቋቁማል፤ ያበረታታል፡፡

             በጀትና ፋይናንስ

             በጀትና  ፋይናንስ  ስለጤና  አገልግሎቱ  እጅግ  ወሳኝ  የሆነ
             ግብዓት ነው፡፡ በዋናነት ዜጎች ለጤና አገልግሎት በሚያወጡት
             ክፍያ ምክንያት ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ ማድረግ የመንግሰት
             ተቀዳሚ  ሥራ  ይሆናል፡፡  ይኼን  እውን  ለማድረግ  ደግሞ

             መንግስት  በአቡጃ  ዲክላሬሽን  የአፍሪካ  አገሮች  በተስማሙት
             መሰረት  ዓመታዊ  የጤናውን  በጀት  የጥቅል  አገራዊ  ገቢው
             (GDP) 15 በመቶ ለማድረግ ይሰራል (አሁን ያለው የጤናው
             በጀት  ከ6  በመቶ  ያልበለጠ  ነው)፡፡  በሁለተኛነት  የጤና
             መድኅንን በመላ አገሪቱ ተግባራዊ በማድረግ ዜጎችን ካላስፈላጊ
             ድንገተኛ  ወጪ  መጠባበቅ  ይሆናል፡፡  በሦስተኛነት  በተለይም

             በጤና መድኅን ታቃፊ መሆን የማይችሉ ዜጎችን የጤና ወጪ
             ለመሸፈን የጤና ታክስን ጨምሮ ፈጠራ የተሞላባቸው የጤና
             ኃብት ማሰባሰብ ሥራዎች ይተገበራሉ፡፡

             የጤና መረጃ፣ ጥናትና ምርምር፤ ዕቅድ አፈፃፀም፣ ክትትልና
             ግምገማ

             አገር  በቀል  ጥናትና          ምርምር  ወቅቱን  የጠበቀና  ተጨባጭ

             የጤና       አግልግሎት         ለማቅረብ        ወሳኝነት        ይኖረዋል፡፡
             በመሆኑም  የአገር  በቀል  መረጃ  ማጠናከር  ትኩረት  ተሰጥቶ




             164    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   161   162   163   164   165   166   167   168   169   170   171