Page 170 - አብን
P. 170

አብን


             በመጠቀም እንዲሁም አገሪቷን ወደ ተሻለ የእድገት ጎዳና ላይ

             ለማሸጋገር በሚያስችል አቅጣጫ ላይ አይደለችም፡፡

             በኢትዮጵያ  ውስጥ  እየተተገበረ  ያለው  ሥርዓተ-ትምህርት
             የፍትኃዊነት፣  የተደራሽነትና  የጥራት  ችግር፣  የትምህርት
             ግብዓት  እጥረት፣  የአስተዳደር  ውስብስብ  ችግሮች  እና
             የፖለቲካ  ተጽእኖ  ያለበት  መሆኑ  ኃቅ  ነው፡፡  የዚህ  ገፊው
             ምክንያት ደግሞ የትምህርት ፖሊሲ ቀረጻው ሂደት ከፖለቲካ
             ተጽእኖ  ነፃ  ያልወጣ  እና  የአገሪቱን  ችግር  ሊፈታ  የሚችል

             ሳይሆን  የአንድን  የፖለቲካ  ቡድን  ሐሳብ  ማስፋፊያ  ሆኖ
             የተዘጋጀ       በመሆኑ        ነው፡፡     በቂ     ውይይትና         ዝግጅት
             ሳይደረግበት፤  ባጉል  ቃላት  ድርደራ  እና  ፕሮፓጋንዳ
             የትምህርት  ፖሊሲውን  በሕዝብ  ላይ  ለመጫን  የሚደረገው
             ሩጫ ውጤት አላመጣም፤ አያመጣምም፡፡ ይህ ሁሉ ዘረፈ-ብዙ
             የሥርዓተ  ትምህርት  ችግር  ሕዝባችንን  በማኅበራዊ  እና

             ኢኮኖሚያዊ  ቀውስ  ውስጥ  አስገብቶ፤  የአገሪቱን  ወጣት
             የወደፊት እጣ-ፋንታ አበላሽቷል፤ እያበላሸም ነው፡፡

             የትምህርት ፖሊሲሲያችን ዓላማዎች
                  መደበኛና  መደበኛ  ያልሆነ  የሥልጠና  ሥርዓት
                    በመዘርጋት፤         የትምህርት         ተደራሽነትን        በሁሉም
                    አካባቢዎች በፍትኃዊነት ማዳረስ፤
                  ትምህርት ያለውን ግለሰባዊና ማህበራዊ ሚና በማሳደግ

                    ምከንያታዊ፣ችግር  ፈቺ  እና  ምርታማ  ማኅበረሰብ
                    መፍጠር፤




             168    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   165   166   167   168   169   170   171   172   173   174   175