Page 169 - አብን
P. 169
አብን
3.2. ትምህርትና ሥልጠና
ትምህርት
ትምህርት የዕድገትና ሥልጣኔ በር መክፈቻ ቁልፍ እንዲሁም
የጥበብ ማማ ላይ መወጣጫ መሰላል ነው፡፡ ት/ት በአንድ
አገር ውስጥ ማኅብረሰቦች በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና
በፖለቲካዊ ዕድገት በብቃት እና በስፋት መሳተፍ ይችሉ ዘንድ
እውቀትንና ክህሎትን የሚሰጥ አንዱና ዋነኛ መሣሪያ ነው፡፡
ት/ት የሰው ልጆችን ግንዛቤ እና ችሎታ በማሻሻል፣ ያለፈውን
ታሪክ በመዘከር፣ አሁንን ከነባራዊ ኩነቶች ጋር በማገናዝብ፣
መጪውንም በማሰብና በመትለም እንዲሁም ከአካባቢያዊ እና
ዓለምአቀፋዊ ዑደቶች ጋር በመላመድ የአገርን የተፈጥሮ
ኃብት፣ ታሪክን፣ ባሕልን እና ወግን በመጠበቅ ከትውልድ ወደ
ትውልድ የሚያሸጋግሩበት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው፡፡
ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የትምህርት ሁኔታ
በአብዛኛው መመዘኛዎች ሲፈተሽ ተማሪዎች ተገቢውን
እውቀት ቀስመውና ክህሎት አዳበረው የችግር ፈቺነትን
ባሕሪና ችሎታ ባለማግኘታቸው የዚህ ዘመን ትውልድ
አብዛኛው በሚባል መልኩ ለችግር ሲጋለጥ ይታያል፡፡
ስለሆነም አገራችን ኢትዮጵያ የሕዝቦቿን ኑሮ ለማሻሻል፣
የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ዕድገት ላይ ቁልፍ
ሚና ለመጫዎት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማበልጸግና
167 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !