Page 173 - አብን
P. 173
አብን
የትምህርት እርከን
ዓለምአቀፍ ደረጃዎችን አገናዝቦ፣ አገርአቀፍና አካባቢያዊ
ጭብጦችንና ፍላጎትን አካቶ ሥርዓተ-ትምህርቱ በየደረጃው
በትምህርት እርከኖች መካከል መወራረስና መደጋገፍ
እንዲሁም ተመጣጣኝነት /ስታንዳርድ/ እንዲጠብቅ ሆኖ
ይዘጋጃል፡፡
መዋለ-ሕፃናት ለመደበኛ ትምህርትና ለአንደኛ ደረጃ
ትም/ት የሚያመቻች ሲሆን ልጆች እሰከ 6 ዓመታቸው
ድረስ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ የዚህ ዋና ዓላማ ሕፃናት
እራሳቸውን በአግባቡ እንዲገልጹ፣ ከሌሎች ጋር የመግባባት
ክህሎትን እንዲያዳብሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያውቁ
የሚያስችል መሰረታዊ የሆነ የትም/ቱ ሥርዓት ይሆናል፡፡
የአጸደ ሕፃናት ትምህርት በዋናነት በግሉ ዘረፍ
ባለሀብቶች፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና
በኃይማኖት ተቋማት የሚያዝ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ
መንግስትም የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
አንደኛ ደረጃ /የመጀመሪያ ደረጃ/ ትምህርት በስድስት
ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን ሕፃናት የመደበኛ ትምህርት
መጀመር ያለባቸው የ7 ዓመት ዕድሜ ሲደረሱ ሆኖ ለ6
171 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !