Page 177 - አብን
P. 177
አብን
የሥራ አመራር ጉዳይን በተመለከተ በየደረጃው
የሚቀመጡ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና አስተዳዳሪዎች
ሁሉ በችሎታቸው፣ በትምህርት ደረጃቸውና
ልምዳቸው፣ እንዲሁም ቦታው የሚጠይቀውን የሥራ
ብቃትና የፈጠራ ችሎታ የሚያሟሉና የአገርና የወገን
ፍቅር እንዳላቸው በማረጋገጥ ብቻ የሚወሰን ይሆናል።
3.4. ማኅበራዊ ዋስትና
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በሕዝብ አገልግሎት
መስሪያ ቤቶችና በግል ባለሃብቶች ሥር የሚተዳደሩ
ሠራተኞች ልዩ ልዩ የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋን
የሚያገኙበት ሕግና ሥርዓት ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ
ይውላል።
በኅመም፣ በአደጋ፣ በዕድሜና በመሳሰሉት ምክንያቶች
የራሳቸውን ሕይወት መምራት ላልቻሉ ዜጎች፣ ለአካል
ጉዳተኞች፣ ወላጅና አሣዳጊ አጥ ለሆኑ ሕፃናት፣ ለጦር
ጉዳተኞችና ብሔራዊ ግዴታዎችን ለተወጡ ዜጎች
ማቋቋሚያ ድጋፍ የሚሆን የማኅበራዊ ዋስትና ፈንድ
ይመሠረታል።
የማኅበራዊ ዋስትናን ሽፋንና መጠን ለማሳደግ የሚያሰችል
ሰፊ የፋይናንስ መሠረት እንዲኖር ዜጎች ከሚያገኙት ገቢና
ከተለያዩ የማኅበራዊ ዋስትና የፋይናንስ ምንጮች
175 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !