Page 180 - አብን
P. 180

አብን


             የተሳሳቱ  የመንግስት  ፖሊሲዎች  ባሳደሩት  ጫና  ምክንያት

             የኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝቧ የምግብ ዋስትናው አደጋ ላይ ያለ
             ሲሆን  ከግማሽ  በላይ  የሚሆነውም  በተለያዩ  መንገዶች
             በሚሰጠው ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ድጎማ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ወደ
             20 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎችም የዕለታዊ ፍጆታዎች ቀጥተኛ
             ድጋፍን የሚሹ እንደሆኑ ይታመናል፡፡

             የምግብ  ዋስትና  ፕሮግራም  ሥር  የሚካተቱ  አንኳር  ጉዳዮች
             የገጠር ቤተሰቦችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣ የእንስሳትና

             አሳ  ኃብት  ልማት  ሥራዎች፣  የተቀናጀ  የመሬት  አያያዝና
             አጠቃቀም፣  የመስኖ  ሥራዎችን  ማስፋፋት፣  የሰው  ኃብትና
             ተቋማት  አቅም  ግንባታ  ሥራዎች፣  የንፁሕ  መጠጥ  ውኃ
             አቅርቦትን  ማሳደግ፣  የማኅበራዊ  ሽግግርን  የሚያሳድግ  ልዩ
             ልዩ  ሥራዎች፣  የገጠር  የፋይናንስ  አማራጮችን  ማስፋት
             እንዲሁም        የገጠር-ከተማ         ማዕከል       ሰፈራ      ፕሮግራምን
             ያካትታል፡፡




               3.6.   የኢትዮጵያ  የሥርዓተ  ምግብ  ችግሮችና  የፖሊሲ
                      አማራጮች

             የማኅበረ  ስነ-ምኅዳር  አማራጭ  ደጋፊዎች  የአግሮ-ኢኮሎጂካል
             ዘዴዎች  ምርታማነትን  በማሳደግ  እና  ማኅበረ-ስነ-ምኅዳራዊ
             አይበገሬነትን        በማጎልበት        የምግብ      ዋስትናን       በዘላቂነት
             ማረጋገጥ         እንደሚቻል          ይሞግታሉ፡፡          በስነ-ምኅዳራዊ
             ብስክስክነት  እና  ማኅበረ-ፖለቲካዊ  አለመረጋጋቶች  ውስጥ

             የአይበገሬነት        ጽንሰኃሳብ        እውናዊ        ሳይሆን       የፖሊሲ
             ፈቃደኝነትን አመላካች ነው፡፡
             178    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   175   176   177   178   179   180   181   182   183   184   185