Page 181 - አብን
P. 181
አብን
የፖሊሲ ፈቃደኘነቱ የሚገለፀውም ከምግብ ዋስትና ጋር
ተያያዥነት ያላቸው ዘርፎች በሙሉ አካታችና የተቀናጀ
የፖሊሲ ዕቅድ በማውጣት ዘላቂነት ባላቸው ስምሪቶች
እንዲገቡ ቁርጠኛ አመራር ሲሰጥበት ነው፡፡ ይህ ሲሆን
ከችግርነት ፈቺነት አቀራረብ ወደ አቅም ገንቢነት መሸጋገር
ይቻላል፡፡
የማኅበረ-ስነ-ምኅዳራዊ ማእቀፍ መዋቅር ሰራሽ የምግብ
ዋስትና ችግሮችን በዘላቂነት እልባት ለመስጠት ትኩረት
ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦችን ለይቷል፡፡ እነሱም፦
አነስተኛ የእርሻ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች
ከምግብ ዋስትና ተጠቂነት ይልቅ እንደሁነኛ
የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ አማራጭ አድርጎ
መመልከትን የገነገነና የተንሸዋረረ ምልከታ
መቀየር፣
መዋቅራዊ ለውጥና ማኅበራዊ ሽግግርን መፍጠር ባልተቻለበት
ሁኔታ አነስተኛ የእርሻ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች
እንደምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ቁልፍነት መያዝ ተገቢነት
አይኖረውም፡፡ በድምሩ እጅግ ሰፊ የሆኑ መልማት የሚችሉ
የእርሻ ቦታዎችን በተበታተነና በተበጣጠሰ መልኩ ከእጅ ወደ
አፍ በሚሆን ስልተምርት እያስቀጠሉ የምግብ ዋስትናን
ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ ስለሆነም አርሶ አደሮች ገበያ ተኮር
የግብርና ምርቶችን በዘመናዊና የተቀናጄ መልኩ እንዲሰሩ
በማድረግ ከነገ ተረኛ ተረጅነት ወደ ነቃ የኢኮኖሚ ዘዋሪነት
የሚያሻግር ፖሊሲ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
179 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !