Page 182 - አብን
P. 182

አብን


                      የምርት አይነቶችን ማብዛት አስቻይ እና ተለዋዋጭ

                        የግብርና ሥርዓት መዘርጋት፣

             እስካሁን  ሲተገበር  ከቆየው  በአንድ  አይነት  ምርት  ያለውን
             ምርታማነት  ማሳደግ  የሚል  ተቸካይ  አቀራረብ  በመላቀቅ
             የአየር  ንብረት  ለውጥ  ተጽእኖን  መቋቋም  የሚያስችሉ፤
             ተለዋዋጭና  የምርት  ብዝኃነትን  ታሳቢ  ያደረጉ  የግብርና
             አማራጮች  የሚዘረጉ  ይሆናል፡፡  ከዚሁ  ጋር  ተያይዘው  ያሉ
             የአሰራር፣  ሕግጋትና  የገበያ  ትስስር  ሁኔታዎችን  ምቹና

             የዘመኑ እንዲሁኖ በትኩረት ይሰራል፡፡

                      የአጭር        ጊዜ      የምግብ        ዋስትና       ችግርንና
                        ተጋላጭነትን         በአደጋ       ዝግጁነትና        መከላከል
                        እንዲሁም  በምግብ  ዋስትና  ማእቀፍ  ምላሽ

                        መስጠት፤

             በትግበራ ላይ ያለውን የሴፍቲኔት መርኃ ግብር በኢኮኖሚ ራስ
             በቅነትን አስቻይ ማእቀፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡


               3.7.   ቋንቋና ባሕል ፖሊሲ
              3.7.1  ባሕል

             ኢትዮጵያ ውብ ባሕሎች ያሏቸው ብሔረሰቦች መኖሪያ ናት፡፡
             በእያንዳንዱ  ብሔረሰብ  ባሕል  ውስጥ  የአንድነት፣  የመፋቀር፣
             የኅብራዊነት  መሠረት  የሆኑ  መልካም  እሴቶች  አሉ፡፡
             የአመጋገብ፣  አለባበስ፣  የኃዘንና  ደስታ  አገላለጽ  ትውፊት፣
             የልጅ  አስተዳደግና  ባሕል  አወራረስ፣  ዘፈን፣  ዜማና  የሙዚቃ

             መሳሪያ፣  የአኗኗር  ዘይቤ፣  ሰው  አክባሪነትና  እንግዳ

             180    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   177   178   179   180   181   182   183   184   185   186   187