Page 187 - አብን
P. 187

አብን


             በኢትዮጵያ የአስተዳደር ክልሎች ከብሔራዊ ቋንቋ በተጨማሪ

             የሥራ  ቋንቋዎች  እንዲኖራቸው  ይደረጋል፡፡  ከሕዝባችን
             ሥልጣኔ  እና  ከአገራችን  ጥንታዊ  ታሪክ  ጋር  ጥብቅ  ቁርኝት
             ያለው  የግእዝ  ቋንቋ  እንዲበለጽግ፣  በትምህርት  ተቋማት
             ሥርዓተ  ትምህርት  ውስጥ  ተካቶ  እንዲሰጥ  እንዲሁም
             የጥናትና ምርምር ማዕከላትና ትምህርት ክፍሎች እንዲከፈቱ
             ይደረጋል፡፡

             የብሔራዊ  ቋንቋ  አስፈላጊነት  ከኢትዮጵያዊ  አንድነት፣  እሳቤና

             አብሮነት  ግንባታ  ጋር  የሚያያዝ  ነው፡፡  ኢትዮጵያውያን
             የየራሳቸውን  አፍ  መፍቻ  ቋንቋ  በየራሳቸው  ፈቃድና
             በመንግስት  ድጋፍ  የማበልጸግና  የማሳደጉ  ጉዳይ  እንደተጠበቀ
             ሆኖ  አማርኛ  ቋንቋ  በሁሉም  የአገራችን  ክፍሎች  ለማለት
             በቀረበ ሁኔታ የሚነገር ቋንቋ በመሆኑ፤ በሁሉም ዘንድ ያለው
             የተግባቦት  አማራጭነት  ሁሉንም  ኢትዮጵዊ  በአንድነት

             ለማግባባትና  ለማቀራረብ  ሁነኛ  ድልድይ  በመሆን  ለአገር
             አንድነትና  ኅብራዊነት  ትክ  የለሽ  ሚና  ይኖረዋል፡፡  ከብዙዎቹ
             የደመቁ  ቋንቋዎች  መካከል  አንድ  የጋራ  ቋንቋ  የኢትዮጵያ
             ብሔራዊ        ቋንቋ      መሆኑን         መቀበል        ኢትዮጵያዊነትን
             ከማጠናከርና  አብሮነትን  በጽኑ  መሰረት  ላይ  ለማንበር
             የሚጫወተው ሚና በዋጋ የሚተመን አይሆንም።


               3.8.   ስፖርት

                  የስፖርት ባሕል እንዲዳብርና የማኅበረሰቦችን መልካም
                    ግንኙነትና  ትብብር  ብሎም  ብሔራዊ  አንድነትንና


             185    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   182   183   184   185   186   187   188   189   190   191   192