Page 189 - አብን
P. 189
አብን
የኪነ-ጥበብ ሥራ ከመንግስት ቁጥጥርና ሳንሱር ነጻ
ይሆናል።
የኪነ-ጥበብ ሥራዎች የኢትዮጵያን የረጅም ዘመናት
ታሪክና ታላቅነት እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ
አንድነትና በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር ልምድ
ለማጠናከር እንዲያግዙ ይበረታታሉ።
ብሔራዊ የአገር ውርስና ቅርስ ለመጠበቅ የሚያስችሉ
ተቋማት ይቋቋማሉ፤ በስራቸውም በሥነ-ቅርስ
ክብካቤና በሳይንሳዊ ጥናት የተደግፉ ጥናቶችን
የሚያካሄዱ ዘርፎች ይኖሯቸዋል።
ለዘመናዊ የኪነጥበብ ሥራዎች ውጤት ማሳያ ዘመናዊ
ሙዝየሞች ይቋቋማሉ።
የአገሪቱን የፈጠራና የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን
የሚያነቃቃ ብሔራዊ የኪነ-ጥበብ አካዳሚ ይቋቋማል።
የአገሪቱን የፎክሎርና ሥነ-ቃላዊ ሥራዎችን፣ አገር
በቀል ጥበባትንና እውቀትን የሚሰበስቡ፣ የሚያጠኑና
የሚሰንዱ እንዲሁም ለልዩ ልዩ መንግስታዊ
ፖሊሲዎች ግብዓት ሊውሉ የሚችሉበትን ሁኔታ
የሚያጠኑ ተቋማት በየባሕል አካባቢው ይቋቋማሉ።
የኪነ-ጥበብና አገር-በቀል ጥበባት ሥራዎች ትእይንቶች
(ኤግዚቢቶች) ማሳያ አዳራሾችና ማእከላት በየባሕል
አካባቢው ይቋቋማሉ።
3.10. ማኅበራዊ ካፒታል
ለአንድ አገር ዘላቂ ኅልውና ኣስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች
መካከል ማኅበራዊ ኃብት ኣንዱ ነው፤ ይህንን ኃብት
መንከባከብ የዜጎችና መንግስት ግዴታ ነው።
187 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !