Page 190 - አብን
P. 190
አብን
በዜጎች መካከል እንዲሁም በዜጎችና በመንግስት
አካላትና ተቋማት መካከል መተማመንና በሕብረት
መስራት እንዲኖር አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል።
የሕዝብ ኃብትና ንብረት ዘረፋና ብክነትን፣ ሙስናንና
በስልጣን መባለግን አጥብቀን እንዋጋለን።
ይቅርታና ፍቅር በዜጎች መሐል እንዲኖር የእምነት
ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች
(መያዶች) ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ይበረታታሉ።
ፓርቲያችን ለሕዝብ ኃላፊነት የሚበቁ ኃላፊዎችን
ለምርጫ ሲያቀርብ፣ ለአገርና ለሕዝብ አሳቢነታቸውን፣
አስፈላጊው የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ብቃትና
ልምዳቸውን፣ እንዲሁም በሙስናና አለአግባብ
ለመበልጸግ በሌሎች ሕገ-ወጥ ተግባራት ውስጥ
የማይዘፈቁ፣ ከወንጀል፣ ዘረኝነትና መሰል መድሏዊ
ጠባያት የጸዱ መሆናቸውን በማረጋገጥና በመወሰን
መታመንን ለመጨመር ይሰራል።
የመረጃ መረቦችን በማብዛት ጤናማና ጠንካራ
ማኅበራዊ ትስስርን (ሶሻል ኔት-ወርክ) እናጠናክራለን።
ፓሊስ፣ የደኅንነት ሰራተኞችና የመከላከያ ሰራዊት
እንዲሁም በሌሎች ልዩ ልዩ መስክ (ማህበራዊ፣
ኤኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወዘተ.) የተሰማሩ
የመንግስት ሰራተኞች ሕዝባዊነትን ተላብሰው
የኅብረተሰቡን የመተማመንና የፍቅር ኃብት
እየተንከባከቡ ሥራቸውን እንዲሰሩ የሚያስችል
ሥርዓት ይዘረጋል።
188 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !