Page 191 - አብን
P. 191
አብን
ጠንካራ የሥራ ባሕልና ሥነ-ምግባር (work ethic)
እንዲኖርና እንዲስፋፋ አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል።
በሕብረተሰቡ አባላት መካከል ማኅበራዊ ትሥሥርና
እምነት እንዲስፋፋ ለማድረግ የሚያስችሉ የማኅበራዊ
ካፒታል ትምህርትና ምርምር ተቋማት ይቋቋማሉ።
3.11. መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች)
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ሰላምና
ልማት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። በመሆኑም የአገር
ውስጥም ሆነ ዓለምአቀፍ መያዶች በሕብረተሰቡ
ልማት ሥራ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ይበረታታሉ።
ለመያዶች ማነቆ የሆኑ ሕጎች ይሻራሉ፤ ለሥራ ምቹ
ሁኔታ ይፈጠርላቸዋል።
መያዶች ገቢያቸውና የተሰማሩበት የሥራ መስክ
እየታየ የሚደጎሙበት መንገድ ይመቻችላቸዋል።
አገር በቀል መያዶች እንዲስፋፉና እንዲያድጉ
ይበረታታሉ።
መያዶች እንዲበረታቱና እንዲጠናከሩ ይደረጋል፤
የአገሪቱን ሕግ አክብረውና ከመንግስት ተጽዕኖና
ጣልቃ-ገብነት ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ይደረጋል።
በሌሎች አገሮች በሰብዓዊ መብት፣ በልማትና በሰላም
ተጨባጭ ውጤት ያስገኙና ለአገር ልማትና እድገት
እንደሚበጁ የሚታመኑ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ
ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ይበረታታሉ።
189 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !