Page 194 - አብን
P. 194
አብን
ለአገራችን ቀጣይ ኅልውናና ሁለገብ እድገት የሴቶች
ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን እናምናለን፤ ለተግባራዊነቱን
በቁርጠኝነት እንሰራለን።
የሴቶችን ማኅበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
ሕይወትና ተሳትፎ ለማሳደግ ልዩ ጥረት ይደረጋል።
የማኅበራዊ ፍትኅ ማካካሻ መርሆች (አፌርማቲቭ
ኣክሽንስ) በመጠቀም ለሴቶች ልዩ የትምህርትና
የተሳትፎ እድሎች እንዲኖሩ ይደረጋል።
በአገሪቱ ፓርላማ ሴቶች ተገቢውን መቀመጫ በመያዝ
እኩልነታቸው በተግባር እንዲረጋገጥ ጥረት ይደረጋል።
3.15. ወጣቶች
ወጣቶች የወጣትነት ጊዜያቸውን ከሱስና አደንዛዥ
እጾች ርቀው ምርታማ በሆነ ሁኔታ እንዲያሳልፉ
ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።
ለልጆች የመጫወቻ ፓርኮች፣ ለወጣቶች መዝናኛና
መናፈሻ ስፍራዎች በየአካባቢው ይገነባሉ።
የትውልድ ክፍተት እንዳይኖር ወጣቱንና ቀዳሚውን
ትውልድ የሚያገናኝ መድረክ በመፍጠር እሴቶችን
እንዲለዋወጡ ይደረጋል።
ወጣቱ በትምህርትና ስነ-ምግባር የዳበረ ዜጋ እንዲሆን
ትኩረት ይደረጋል።
ወጣቱ ትውልድ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁና ውጤታማ ተሳትፎ
192 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !