Page 192 - አብን
P. 192
አብን
በልዩ ልዩ ተጽእኖዎች ምክንያት የተዘጉ አገር በቀልና
ዓለምአቀፋዊ መያዶች እንዲከፈቱ ይደረጋል፤ ሌሎች
አዳዲስ መያዶችም እንዲመሰረቱ እናበረታታለን።
በተለይ በዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት እንዲሁም
በግብርና፣ በጤናና ትምህርት ልማት ዘርፍ ለሚሰሩ
መያዶች ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
3.12. መገናኛ ብዙኃን
የፓርቲያችን የፓለቲካ ፍልስፍና ከሆኑት ጉዳዮች
አንዱ ብዝኃነት ሲሆን፣ ብዝኃነት ከሚገለጽባቸው
አንዱ የመገናኛ-ብዙኃን (ሚዲያ ብዝኃነት) ነው።
በመሆኑም የብዙኃን መገናኛዎች የአገሪቱን ብሔራዊ
አንድነትና የጋራ እሴቶች ለማጠናከር ይሰራሉ፤
ባሕላዊና ኃይማኖታዊ እኩልነትንና ሰላማዊ አብሮነትን
አክብረው፣ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተላብሰው እንዲሰሩ
ይበረታታሉ።
የብዙኃን መገናኛዎች ከመንግስት ተጽእኖና ወገናዊነት
ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ይደረጋል።
የፕሬስ ነጻነት የተረጋገጠ ነው።
ሚዲያው ብዝኃነትን ባሕል እንዲያደርግ ይደረጋል።
የመንግስትና የግል ፕሬስና ሚዲያ የኢትዮጵያን ሕዝብ
ከዳር እስከዳር እንዲደርስ ይደረጋል።
የግል ፕሬስ፣ የግል ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች
እንዲከፈቱ ይበረታታል።
190 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !