Page 197 - አብን
P. 197
አብን
ምዕራፍ 4
ብሔራዊ ደኅንነትና የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ
4.1 ሰላም፣ ጸጥታና መረጋጋት
4.1.1. የትናንቱ የአገርና የዜጎች የሠላም፤ የጸጥታና
የመረጋጋት ሁኔታ ሲዳሰስ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ‹‹ሠላም፤ ፀጥታና
መረጋጋት›› ለአንድ አገር ኅልውናና ኁለንተናዊ እድገት
ዋስትና በመሆናቸው የሕዝብ ስልጣን የያዘ መንግስት
በቅድሚያ ሊያረጋግጣቸው የሚገቡ ቁልፍ ጉዳዮች
መሆናቸውን አበክሮ ይገነዘባል፡፡ ዜጎች በአገራቸው የተረጋጋ
ሕይወትን ሊመሩና በኁለንተናዊ ተሳትፏቸው ለአገር
የሚጠበቅባቸውን ያበረክቱ ዘንድ የተረጋጋ ሠላም ብሎም
ሕግና ሥርዓት የሰፈነበት ሥርዓተ-መንግስት መፈጠር
አለበት፡፡ በአንድ አገረ መንግስት ስር ሠላምና መረጋጋትን
ለማስፈን የፍትኅ፣ የመከላከያና የፖሊስ ተቋማት ከፖለቲካዊ
ወገንተኝነት በጸዳ መልኩ ለሁሉም ዜጎች በእኩልነት ላይ
የተመሰረተ ግልጋሎትን መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመሆኑም
እነዚህ ተቋማት ባለቤትነታቸው የሕዝብ ብቻ ሆነው የአገርና
የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ሊያስጠብቁ በሚችሉበት ተቋማዊ
አወቃቀር መመስረት ይኖርባቸዋል፡፡
195 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !