Page 201 - አብን
P. 201
አብን
ፖሊሲዎች ማስፈጸም በፊት የመፈፀሚያ ሜዳውን ሰላማዊና
የተረጋጋ ለማድረግ መላው የአገሪቱን ሕዝቦች ያማከለ
ብሔራዊ እርቀ ሰላምና አገራዊ መግባባትን ይፈጥራል፡፡
የአፈፃፀም መመሪያዎችና ድንጋጌዎችንም አውጥቶ ተግባራዊ
ያደርጋል፡፡
አብን በአገሪቱ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም
የዜጎች የደኅንነት ዋስትና ይኖር ዘንድ ከብሔራዊ እርቅና
መግባባት ባሻገር በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በትኩረት የሚሰራ
ይሆናል፡፡
በክስተቶችና በሁኔታዎች ያልተገደበ፣ የተጠና፣ ስልታዊና
ተከታታይ የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ሥራዎችን
መስራት፤
ውስጣዊ ግጭቶችን ሊቀሰቅሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ
የቅድመ-ጥንቃቄ ተግባር መፈፀም፤ከተከሰቱም
ለመቆጣጠርና ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራሥርዓት
መዘርጋት ፤
በሕዝቦች መካከል አብይ የግጭት መንስኤ ለሆኑት
የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ታሪክና የታሪክ ማስረጃን፣
ነባራዊ ሁኔታንና የሕዝብን ፍላጎትን መሰረት ባደረገ
መልኩ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት፤ ብሎም ተመሳሳይ
ችግሮች እንዳይከሰቱ ሂደቱን የሚከታተል ገለልተኛ ተቋም
ማቋቋም፤
199 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !