Page 204 - አብን
P. 204
አብን
ከአገር ውስጥ ሰላም እጦት በተጨማሪ የኢኮኖሚ መዳከም፣
ድህነትና የዴሞክራሲ መቀጨጭ አገሪቱን የደኅንነት ስጋት
ተጋላጭ ያደርጋል፡፡ ታሪካችን እንደሚያረጋግጠው የኢትዮጵያ
የውስጥ ተጋላጭነት በአገሪቱ ግዛታዊ አንድነትና
በጸጥታ/በደኅንነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ካሳደሩ ምክንያቶች
አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ውስጣዊ የደኅንነት ችግሮቻችን
ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጥሮ ኃብትና የድንበር ውዝግብ ላላቸው
ክልላዊ የፖለቲካ ኃይሎችና ወኪሎቻቸው ጣልቃ ገብነት
እድል በመስጠት የአገሪቱን ሰላም እንዳይረጋጋ ለማድረግ በር
ይከፍትላቸዋል፡፡
በመሆኑም የአብን የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ የሕዝቦችን
የውስጥ ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ ትልቅ ትኩረት
ሰጥቶ ይሰራል፡፡ የሰላምና ደኅንነት ፖለሲና ስትራቴጂያችን
ከላይ የተዘረዘሩትን የውስጥ ተጋላጭነቶች በመቀነስና
የአገሪቱና የሕዝቡን ፍላጎት ማስጠበቅ የሚያስችል የውጭ
ግንኙነት (የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊ ዲፕሎማሲ
ወይም ዲተረንስ) የመደራደር አቅም የማጎልበቱን ሂደት
ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡
202 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !