Page 209 - አብን
P. 209
አብን
ደኅንነት አማካሪ ኮሚቴ፣ መከላከያ እና የደኅንነት ተቋማት
የውስጥ ኦዲት ክፍሎች)
3) የዲሞክራሲ ተቋማት ለምሳሌ ዋና ኦዲተርና የሰብዓዊ
ኮሚሽን
4) በሲቪክ ማኅበራት (Oversight by Civil Societies)
በጸጥታው ተቋማት ሥርዓት ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ
የሚመለከት ነው፡፡ የእነዚህ አካላት የተሳትፎ ድርሻ በተለያየ
ደረጃ እየተመጠነ የጸጥታ ተቋማቱ አሰራር ግልጽነትንና
ተጠያቂነትን ለማስፈን ዴሞክራሲያዊ ክትትል፣የፍተሻና
የማስተካከያ ስራዎች ይፈቀዳሉ፡፡
4.2.2 ውጫዊ የሰላምና ደኅንነት ትኩረት
የአገር ውስጥ ሰላምና ደኅንነትን ከመጠበቅና ከማጎልበት ጎን
ለጎን በጎረቤት አገራትና በዓለምአቀፍ የሚካሄዱ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚያዊና ባሕላዊ ተፅእኖዎችና ጣልቃገ ብነቶችን ለይቶና
አጥንቶ ተገቢ የሆነ ፖሊሲ መቅረጽ ግድ ነው፡፡ ምክንያቱም
የአንድን አገር ሰላምና ደኅንነትን ከሚያደፈርሱ ጉዳዮች ውስጥ
ውጫዊ ምክንያቶች የጎላ ቦታ የሚሰጣቸው መሆኑ ነው፡፡
የኢትዮጵያም የሰላምና ደኅንነት ሁኔታ ከውጭው ዓለም
ተጽዕኖ ነጻ ስለማይሆን ሁኔታውን ከውጭ ወደ ውሰጥ ማየት
የሚያስችል የፖሊሲ አቅጣጫ የማስቀመጡ ሥራ የምርጫ
ጉዳይ አይደለም፡፡
የውጪ ግንኙነት ፖሊሲያችን በትኩረት የሚያያቸው የአገርን
ሁሉአቀፍ ሥርዓት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥለውን የሳይቨር
207 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !