Page 207 - አብን
P. 207
አብን
የአዛዦች የአመዳደብ ሥርዓት በግልጽ መስፈርት (ሙያን
ማዕረግን ይጨምራል፣ ልምድን/አገልግሎትን፣ ክህሎትን
ቋንቋን ይጨምራል) እንዲከናወን፤እንዲሁም ሰራዊቱ ክልላዊና
ዓለምአቀፋዊ የሰላም ማስጠበቅና ማስከበር ተልዕኮዎችን
በብቃት የሚወጣ ተቋማዊ ቁመና እንዲላበስ ይሰራል፡፡
ሠ) የደኅንነትና የመረጃ ተቋማት የአሰራር አቅጣጫ
አብን ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ የመከላከያ የመረጃ ክፍል፣
የፌደራል ፖሊስ እና የክልሎች የመረጃና ደህንነት ተቋማት
ሥርዓትና የአሰራር ስልቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ እነዚህ
የመረጃና ደኅንነት ተቋማት የእርስ በእርስ ግጭቶችን
መነሻዎችና ሂደቶችን፣ ከስደተኞች ጋር የተያያዘ የጸጥታና
የጦር መሳሪያ ዝውውር ሁኔታዎችን፣ ሽብርተኝነትንና
አክራሪነትን፣ ክልላዊ የሰላም ሁኔታንና የኒኩለር የጦር
መሣሪያ ጉዳዮችን ከአገር ደኅንነት አንጻር የመገምገም
ኃላፊነት የሚሸከሙ ይሆናል፡፡
የአብን የፖሊሲ አቅጣጫ የኢትዮጵያ የደኅንነትና መረጃ
ተቋማት የዘመኑና ለቅድመ መከላከል ብቁ ግብዓት እንዲሆኑ
የማስቻል ዓላማ ያለው ነው፡፡ ተቋማቱ ይህን ኃላፊነት በስኬት
እንዲወጡ ብቃታቸውን ማሳደግ የሚያስችሉ የእውቀት እና
የቁሳቁስ ግብዓቶች የማሟላት ሥራ ትኩረት የሚሻ መሆኑን
ስለሚያምን በጥናት ላይ የተመሰረተ የማጎልበት ሥራን እውን
ያደርጋል፡፡ ይህም በክልል (በአፍሪካ ቀንድ) እና በዓለምአቀፍ
205 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !