Page 210 - አብን
P. 210
አብን
ጥቃት፣ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች፣ ሽብርተኝነት፣ ድንበር
ተሸጋሪ የጋራ ኃብትና የዜጎች የሕገ-ወጥ ስደት ጉዳይ
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከአገሪቱ ሰላምና ደኅንነት ጋር
ግንኙነት አላቸው፡፡ ኢትዮጲያ የራሷን ጠንካራ የአገር
መከላከያና የደኅንነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ በማዘመን
አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት ማስፈን የውጪ ግንኙነት
ፖሊሲው ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡
ቀጠናዊ የሰላምና ደኅንነት ትኩረት
ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኤርትራና ከሱዳን ጋር
የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎች የሕገ-ወጥ ድንበር ተሻጋሪ
ወንጀሎች ቀጠና መሆናቸው በጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ ከደቡብ
ሱዳን ድንበር በኩል የጦር መሣሪያ ዝውውርና ገደብ አልባ
የስደተኞች መጉረፍ፣ የድንበር ግጭትና የይገባኛል ውዝግብ
እንዲሁም ከሶማሊያ ድንበር ዘለል የሕገ-ወጥ ታጣቂዎች
እንቅስቃሴ ለቁጥጥር ያዳገተ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም
ከአሁን በፊት ሲደረግ የነበረው ልቅ የድንበር እንቅስቃሴና
የሁለት አገር ዜግነት ብሎም የስደተኞች ፍሰት ሥርዓት
የሚበጀለት ይሆናል፡፡ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከፌደራሉ
መንግስት ጋር በመተባበር የድንበር እንቅስቃሴን ሰላማዊነት
እውን እንዲያደርግ አደረጃጀት በመፍጠር የተዋሳኝ አገራትን
የጋራ ጥቅም የሚያረጋግጥ የጋራ የጸጥታና የኢኮኖሚ
የትብብር ማዕቀፎች ይዘረጋሉ፡፡
208 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !