Page 215 - አብን
P. 215
አብን
14. የውጭ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ
ሽግግር ማስፋፋት፣ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን
ማበልጸግና ልምድ መጋራት እንዲሁም በሌሎች
ዘርፎች ከውጭ አገራትና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር
መተጋገዝን መሰረት ያደረገ የውጭ ግንኙነትና
የዲፕሎማሲ ሂደትና አፈጻጸም አትኩሮ መስራት፤
15. ጠንካራ የሰላም ማስጠበቅና ማስከበር ተቋማትን
እውን በማድረግ በዓለምአቀፍ መድረኮች ተወዳዳሪ
የሆነ የመረጃ ቋትን መገንባት፤
16. የግልጽ ምንጭ መረጃን አበክሮ በመጠቀም የአገራት
እንዲሁም የተለያዩ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና
ዓለምአቀፋዊ ተቋማት መሪዎችና ወኪሎቻቸው
የሚያንጸባርቋቸውን አቋሞች፣ የሚያዘጋጇቸውን
ሰነዶችና የሚያሳዩአቸውን ባሕሪያት በመከታተል፣
ተንትኖ በውል ለመረዳት የሚያግዝ ተቋምን እውን
ማድረግ፤
17. የሳይበር ደኅንነት አደረጃጀቶችን ተቋማዊነት
ማጠናከር፣ በሳይበር የተከላካይነት አቅምን
ማረጋገጥና ተቋሙ የአገር ደኅንነት ማስጠበቅ ላይ
እንዲወሰን ማድረግ፤
18. ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በተለይ ከስደተኞች
ጋር የተያያዘ የጸጥታና የጦር መሣሪያ ዝውውር
ሁኔታዎችን፣ ሽብርተኝነትን፣ ክልላዊ የሰላም
ሁኔታንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከአገር ደኅንነት አንጻር
የመገምገም ተቋማዊ ብቃትን ማሳደግ፤
213 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !