Page 216 - አብን
P. 216
አብን
19. በቅርቡ የተዋቀረው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል
ኅልውና በኢትዮጵያ ፍላጎት ላይ ብቻ የሚወሰን
ባለመሆኑ የክልላዊ ዲፕሎማሲ ተጽኖ ፈጣሪነትን
በማሳደግ የባሕር ኃይልን የማደረጃት እንቅስቃሴ
አጠናክሮ ማስቀጠል፤
20. ወታደራዊ የውጭ ስልጠናዎች፣ የቴክኒክ እገዛዎች
እና የቁሳቁስ ድጋፎች እያደገ ከሚመጣው የሰላምና
የደኅንነት ሥራዎች እንዲጣጣም የፍላጎት ዳሰሳ
ቅድሚያ እንዲሰጠው ማድረግ፤
21. የወታደራዊ አታቼ አመዳደብ ወታደራዊ የሙያ
ብቃትንና የአካዳሚዊ አውቀትን መሰረት እንዲደርግ
መርኅ ማጽደቅ፤
22. ድንበር ዘለል የወንጀል ድርጊቶችን በተመለከተ
ከኢንተር-ፖል ጋር መናበብና መደጋገፍ፣
የኤክስትራዴሽን ወይም የወንጀለኛ ቅይይር
ውሎችን ማስፋት፤
23. ከድንበር ግጭቶች ነጻ ለመሆን የዓለምአቀፍ
ሕግጋትንና የዲፕሎማሲ መርሆችን በመመርኮዝ
መስራት፤
24. የመከላከያና ደኅንነት ተቋማት አሰራሮች ግልጽነትና
ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የሕግና የአፈጻጸም
መርሆችን ማዘጋጀት፤ ግልጽ በሆነ አግባብ
ሚስጥራዊ የሆኑና ሚስጥራዊ ያልሆኑ አሰራሮች
በሕግ ተደንግገው እንዲታወቁና የተቋማቱ
አሰራሮችና የቁሳቁሶች የውጭ ግዥ በዴሞክራሲያዊ
ቁጥጥር/ክትትልና በማስተካከል መርኅ (principles
214 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !