Page 221 - አብን
P. 221

አብን


             የተለያዩ  የግንኙነት  ስልቶችን  መጠቀም  አስፈላጊ  መሆኑን

             ያምናል፡፡  ከእነዚህም  በውጭ  ጉዳይ  ሚኒስቴር  በኩል፣
             የአመራሮች  የውጭ  ዲፕሎማሲ  ማከናወን፣  በአገር  ውስጥ
             ያሉ  የውጭ  አገር  ተቋማትንና  ኢምባሲዎችን  መገናኘት፣
             የተለያዩ  ሚዲያዎችን  በመጠቀም  ለዓለምአቀፉ  ማኅበረሰብ
             ተደራሽ መሆንና ወቅቶችን ያገናዘቡ የፕሮፓጋንዳ መረጃዎችን
             ማሰራጨት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ዲፕሎማሲው የሚፈጸመው
             በኮንፈረንስ፣  በብዙዮሽና  በሁለትዮሽ  ድርድሮች  ነው፡፡  ጥቅሉ
             ብዛት  ያላቸው  የውጪ  ግንኙነት  ፖሊሲ  መተግበሪያ

             መሣሪያዎች  ያሉ  ቢሆንም  በአገራችን  ተጨባጭ  ሁኔታ
             የፖለቲካ  ዲፕሎማሲ፣  የኢኮኖሚ/የምጣኔኃብት/፣  የመከላከያ
             ኃይልና ሚዲያዎች በሚል ልንከፍለው እንችላለን፡፡

             ሀ) የኮንፈረንስ የዲፕሎማሲ ሥራ/ multilateral diplomacy)


             በዓለምአቀፍ የፓርላማ ትብብር ማዕቀፍ የሚከወን ዲፕሎማሲ
             (የዓለም       አቀፍ      conference       and     parliamentary
             diplomacy)፣  የአገሪቱ  ከፍተኛ  አመራሮች  እንደየአስፈላጊነቱ
             የውጭ  ጉዞና  ኮንፈረንስ  በመሳተፍ  እና  ከሌሎች  አገራት
             መሪዎች  ጋር  በቡድንም  ሆነ  በተናጠል  ውይይት  እና
             ከዓለምአቀፍ ተቋማቶች ጋር በመገናኘት የአገሪቱን የብሔራዊ
             ጥቅም  ዓላማ  ማስፈጸም  የሚያስችሉ  የድጋፍ  ኃይልን
             የሚያጠናክሩና  ገጽታ  ግንባታ  ተግባራት  ማከናወን  ትኩርት

             የሚሰጠው የውጭ ግንኙነት ማስፈጸሚያ ስልት ነው፡፡
             የሁለትዮሽ  ዲፕሎማሲ፦  የሁለትዮሽ  ዲፕሎማሲ  ከተለያዩ
             አገራት  ጋር  እንደየአስፈላጊነቱ  ሕጋዊ  /በፓርላማ  የሚጸድቅ/


             219    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   216   217   218   219   220   221   222   223   224   225   226