Page 225 - አብን
P. 225

አብን


             የሚሰራጩ  የውጭ  ግንኙነትን  የሚመለከቱ  መግለጫዎችና

             ጽሁፎች  በውጭ  ጉዳይ  ሚኒስትር  ሕዝብ  ግንኙነት  ክፍል
             እየተዘጋጁ  የሚሰራጩ  ይሆናል፡፡  ማኅበራዊ  ሚዲያው
             ከውጭው  ዓለም  ጋር  የሚደረገውን  ሁሉንአቀፍ  ግንኙነት
             በሚያሳልጥ፣  የአገሪቱን  ገፅታ  በሚገነባና  ተጽዕኖ  መፍጠር
             በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል ይተኮርበታል።


             4.3.3 የባሕርበር እና የወደብ አገልግሎት


             ኢትዮጲያ  አገራችን  ቢያንስ  ከጥንታዊቷ  የአክሱም  ዘመን
             ጀምሮ  ከውጭው  ዓለም  ጋር  የምታደርገው  የፖለቲካ፣
             የባሕል፣       የንግድና       የዲፕሎማሲ          ግንኙነቶች        በሕንድ
             ውቅያኖስና  በቀይ  ባሕር  ዳርቻ  በነበራት                        የባሕርበር
             አማካኝነት  ነበር፡፡  በወቅቱ  አገርአቋራጭ  ንግድ  ስታካሄድ

             የነበረው ሲሆን እንደበርበራ ሀዶሊስ (ሚሶዞያ) ዘይላ እና የቀይ
             ባሕር አካባቢ የበሕር በሮችን ትጠቀም የነበረው የራሷ የግዛት
             አካል በማድረግ ነበር።

             ከአክሱም ዘመን  ጀምሮ የኢትዮያ  ገናነትና  ውድቀት  በወደቦች
             ላይ  በነበራት  ቁጥጥር  ተፅእኖ  እንዳደረበት  አይካድም፡፡
             በየጊዜው  በአካባቢው  የሚነሱ  ኃይሎች  እነኝህን  የወደብና
             የባሕር  በሮችን  ለመቆጣጠር  ከኢትዮጵያ  መንግሥት  ጋር

             ጦርነትና  ግጭቶች  እያደረጉ  አልፎ  አልፎም  በሮቹን
             እየተቆጣጠሩ  እንደነበር  ከታሪክ  እንረዳለን፡፡  የሩቁን  ብንተው
             እ.ኤ.አ  የ1952  የተባበሩት  መንግስታት  ውሳኔ  የኢትዮጵያን


             223    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   220   221   222   223   224   225   226   227   228   229   230