Page 224 - አብን
P. 224
አብን
የማደረግን (deterrence) ዓላማ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ለአገራችን ደኅንነት ስጋት የሚሆን ማንኛውም አካል
በድርድርና በመነጋገር የመፍታት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ
ይህ ካልተሳካና ውጤት ካላመጣ ብሎም የደኅንነት ስጋት
ከተጋረጠ የመከላከያ ኃይል እንደአስፈላጊነቱ ጥቅም ላይ
ይውላል፡፡
ረ) ሚዲያዎች
ሚዲያዎች ሲባል በዓይነት እና በይዘት የሚለያዩ ሲሆኑ
የሕትመትና የኤሌክተሮኒክ ሚዲያዎች እና የማኅበራዊ
ሚዲዎችን ያካትታል፡፡ የውጭ ግንኙነቱን ስራ ለመከወን
በግልና በመንግስት ሚዲዎች መጠቀም የሚቻል ሲሆን
ፓርቲው/ሲመረጥ/ በቀጥታ ለእነዚህ ተቋማት የውጭ
ግንኙነት አቋሙን የሚገልጽበትን መልዕክት ለሕትመት
እንዲበቃ ከማድረግ በተጨማሪ ምሁራን ተሳታፊ ሆነው
ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ይሰራል፡፡ ይህን መሰል ከመንግስት
ኃላፊነት ውጭ በሆኑ ምሁራን የሚያደርጉት የመንግስት
ማበረታቻ ይደረጋል፡፡
ከላይ በተገለጹት የመገናኛ ዘዴዎች የተለያዩ ቋንቋዎችን
መጠቀም ተደራሽነትን እንደሚያሳድግ እሙን ነው፡፡ በዚህ
ረገድ የሚሰራጨውን ኃሳብ ቢያንስ በእንግሊዘኛ፣
በፈረንሳይኛና በአማርኛ በማዘጋጅት ተደራሽ መሆን የሚቻል
ሲሆን በተጨማሪም ለውጪ ግንኙነቱ ሥራ ሌሎች
ቋንቋዎችን እንደየአስፈላጊነቱ መጠቀም ይቻላል፡፡ በየጊዜው
222 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !