Page 222 - አብን
P. 222

አብን


             ስምምነቶች  በመፈራረም፣  በመደራደር  እና  ዘርፈ  ብዙ

             ግንኙነቶች የመመስረት የዲፕሎማሲ ሥራ ይከናወናል፡፡

             ለ) የሕዝብ ዲፕሎማሲ (public diplomacy)

             ይህኛው  ዘርፍ  ከመንግስታት  የሁለትዩሽ  ወይም  የብዙዮሽ
             ግንኙነት  በተለየ  በተለያዩ  አገራት  ያሉ  ሕዝቦች  እርስበእርስ
             መተማመንንና  መግባባትን  የሚያጠናክር  ሆኖ  የተለያዩየ
             ማኅበረሰብ  ክፍሎችንና  አደረጃጀቶችን  በመጠቀም  የሚፈጸም

             የዲፕሎማሲያዊ  ትስስር  ሂደት  ነው፡፡  አተገባበሩ  መንግስት
             ድጋፍ የሚያደረግበት የባሕል ትስስር መፍጠር፣ በሥነ-ጥበብ
             የታገዘ  ግንኙነት፣  የትምህርት  ነክ  ግንኙነት  (ስኮላርሽፕ  እና
             ፌሎውሽፕ)፣  የግለሰቦች  (በተለይ  ኢሊቶች)  እና  የሚዲያ
             አካላትየሚሳተፉበት ሂደት ነው፡፡


             ሐ) የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና ትስስር

             በተለይ  ከጎረቤት  አገራት  እና  የተለያዩ  የንግድ  ትስስርና
             የተፈጥሮ  ኃብት  ተጋሮት  ካላቸው  የአፍሪካ  አገራት  ጋር
             መሰረተልማቶችን  በትብብር  በመስራት  እና  የተጀመሩትን
             በማጠናከር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲጠነክሩ ይሰራል፡፡
             ሌሎች  አገራት  ከኢትዮጵያ  ሊያገኙት  የሚችሏቸው  በርካታ
             የኢኮኖሚ        ጥቅሞች        በመኖራቸው         (የመደራደር         አቅም

             የሚፈጥሩ ናቸው)  ዘርዝር የስትራቴጂ ማስፈጸሚያ ስልቶች
             ነድፎ  በማስፈጸም  የኢኮኖሚ  ዲፕሎማሲው  እድገት  እውን
             ለማድረግ ይሰራል፡፡


             220    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   217   218   219   220   221   222   223   224   225   226   227