Page 220 - አብን
P. 220
አብን
በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን መብታቸው
ተከብሮ እንዲኖሩ የሚያስችሉ ስምምነቶች እንዲፈረሙ
ማድረግ፤
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የውጭ አገራት መንግሥታት
እንደራሴዎች፣ ቆንስላዎችና የዓለምአቀፍ መንግስታዊ
ድርጅቶች ወኪሎችን በመጠቀም ወጭ ቆጣቢ
ዲፕሎማሲማከናወን፤
በአገሪቱ ቱሪዝም እንዲስፋፋ፣ ከዚህም ዜጎች
የሚገባቸውን ፍትኃዊ ተጠቃሚነት እንዲያገኝ
መስራት፤
ኢትዮጵያ ከድህነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ጥረት
የሚያግዝ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ የውጭ ንግድ፣
የውጭ የልማት ፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎች
ማስገኘትና ከሂደቱም ሆነ ከውጤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ
በእኩልነት እንዲጠቀም ማስቻል፤
የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚያሻክሩ በፖለቲካ
የተቃኙ አስተምሮዎችና የአንድን ሕዝብ ታሪክና ገጽታ
የማጠልሸት ዓላማ የነበራቸው ትርክቶች እንዲታረሙ፣
ይህንም የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ መስራት
ናቸው፡፡
4.3.2 የውጭ ግንኙነት መተግበሪያ ስልቶች (Foreign policy
Instruments)
አብን ከውጭው ዓለም ጋር የሚደረገው ግንኙነት ፍሬያማ
እንዲሆን እንደየሁኔታው የስልቶቹን አዋጭነት በመፈተሽ
218 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !