Page 218 - አብን
P. 218

አብን


                    የኢትዮጵያን  ጥቅም  አደጋ  ላይ  የሚጥሉ  የውጭ

                    አገራት ድርጊቶችን በዋዛ ያለማየት፤
                  ከየትኛውም  የዓለም  ሕዝብ  ጋር  የሕዝብ  ለሕዝብ
                    ግንኙነትን  ማዳበር  እና  እያደገ  የሚመጣ  የማኅበራዊ፣
                    የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትብበሮችን ማድረግ፤
                  የአካባቢያዊና ዓለምአቀፋዊ              ግጭቶችና ያለመግባባቶች
                    በሰላማዊ  መንገድ  የሚፈቱበትን  አማራጮች  አሟጦ
                    መጠቀም፣ በቅድመ መከላከል ስልት ላይ ማተኮር፤
                  ኢትዮጵያ  ከምትፈጽመው  የውጭ  ትብብር  ከሚገኙ

                    ጥቅሞች  ዜጎች  በእኩልነትና  በፍትኃዊነት  ተጠቃሚ
                    መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
                  አገሪቱ ካላት የሕዝብና እምቅ የተፈጥሮ ኃብት አንጻር
                    በሰላም ግንባታ፣ ሰላም ማስከበርና ግጭት አፈታት ላይ
                    መሳተፍ፤


             ለ) የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ግብ

             የአብን  የውጭ  ፖሊሲ  የሚቃኘው    «የአንድ  አገር  የውጪ
             ግንኙነት  ፖሊሲ  ከሕዝብ  መሰረታዊ  ጥቅሞችና  ፍላጎቶች
             ይመነጫል» በሚለው መሰረታዊ መርኅ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም
             የአብን  አማራጭ  የውጪ  ጉዳይ  ፖሊሲ  ኢትዮጵያ  ከሌሎች
             አገራት፣  ከአሕጉራዊና  ዓለምአቀፋዊ  ተቋማትና  ሌሎችም
             ተሳታፊዎች  ጋር  በሚደረጉ  ግንኙነቶች  ላይ  የራሷንና

             የእነዚህን  ተዋናዮች  ባሕሪና  ተግባራት  በመግራትና  ቅርፅ
             በማስያዝ፣  የውጪ  ግንኙነቶች  ወንድማማችነትንና  ትብብርን
             መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ በማስቻል፣ የኢትዮጵያዊያንን ዘላቂ


             216    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   213   214   215   216   217   218   219   220   221   222   223