Page 213 - አብን
P. 213

አብን


                    4.  የውጭ  ግንኙነትና  የዲፕሎማሲ  ባለሙያዎችን

                        ምልመላ፣  ምደባና  ድልድል  በእውቀት፣ክህሎትና
                        ልምድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግ ዘርፉን
                        ከሙያነትና  ከአገር  ጥቅም  አንጻር  ብቻ  እንዲታይ
                        የሚያስችል         መዋቅር፣        አደረጃጀትና        አሰራር
                        መዘርጋት፤
                    5.  ትብብርን  ከኢኮኖሚ  ማዕዘን  ብቻ  ሳይሆን  ሰዋዊና
                        ሰብዓዊ  የውጭ  ግንኙነትና  የዲፕሎማሲ  ሂደትና
                        ተግባር መዘርጋት፤

                    6.  የሰላም       ዲፕሎማሲን           ማጎልበትና         ለሕዝብ
                        ዲፕሎማሲ          /public    diplomacy/       ትኩረት
                        መስጠት፤
                    7.  ወቅታዊ       ዓለምአቀፍ        ለውጦችንና         ክስተቶችን
                        መሰረት  ያደረገ  የውጭ  ግንኙነትና  ዲፕሎማሲ
                        እንዲኖር  ማድረግ፤  ከአዳዲስ  አገራዊ፣  ቀጠናዊ፣

                        አሕጉራዊና  ዓለምአቀፋዊ  ስጋቶች፣    ተለዋዋጭ
                        ኩነቶችና የትኩረት መስኮች መካከል የዓለም አቀፍ
                        ንግድ፣  ልማት፣  የስደተኞች  ጉዳይ፣  የሰብዓዊ
                        እርዳታ፣ የውኃ ፖለቲካ (hydro politics)፣ የአየር
                        ንብረት  ለውጥና  ድርቅ  የመሳሰሉትን  ሁነኛ  ቦታ
                        መስጠት፤
                    8.  አገራዊ  ሁኔታዎችንና  ፖሊሲዎችን  እንዲሁም
                        መለዋወጦችን ያገናዘበ ማድረግ ማለትም የለዘብተኛ

                        ሊበራል የፖለቲካ-ኢኮኖሚ መርኅን መሰረት ያደረገ
                        እንዲሆን ማድረግ፤




             211    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   208   209   210   211   212   213   214   215   216   217   218