Page 208 - አብን
P. 208
አብን
ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የመረጃ ተቋማቶችን ገንብቶ ማዘመን
የሚመለከት ነው፡፡
በሌላ በኩል ብሔራዊ የሳይበር ተቋማት የፖለቲካ ድርጅቶች
መሣሪያነት መሆኑ እንዲቀር ይደረጋል፡፡ የመከላከያ፣ ብሔራዊ
ደኅንነትና የመረጃ ተቋማት ዜጎችን እና ተፎካካሪ የፖለቲካ
ድርጅቶችን መሰለያ መሆናቸው እንዲቀርና የአሰራሩ ተቋማዊ
ባሕል እንዲዳብር ይደረጋል፡፡
ረ) የደኅንነትና የመከላከያ የአሰራር ሥርዓት ግልጽነት
የመከላከያ እና ደኅንነት ተቋማት አሰራሮች ግልጽነት እና
ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የሕግ እና የአፈጻጸም መርሆችን
ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ግልጽ በሆነ አግባብ ሚስጥራዊ
የሆኑና ሚስጥራዊ ያልሆኑ አሰራሮች በሕግ ተደንግገው
እንዲታወቁና የተቋማቱ አሰራሮችና የቁሳቁሶች የውጭ ግዢ
ሂደቶች በዴሞክራሲያዊ በቁጥጥር/በክትትልና በማስተካከል
መርኅ (principles of democratic over-sight to the
defense forces) እንዲቃኙ የማድረግ ሥራ ይሰራል፡፡
ይህ ሲባል፦
1) የፓርላማ የመከላከያና ደኅንነት ቋሚ ኮሚቴ
(Parliamentary Oversight) ፣
2) የመንግስት አስፈጻሚ አካላት (Oversight by the
executive body፡- ለምሳሌ የጠቅላይ ሚኒስተር የመረጃና
206 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !